AleHig Law Office is a premier legal office specializing in a wide range of legal services in Ethiopia, Addis Ababa, including government engagement, corporate law, investment, commercial law, business law, property disputes, family law, succession, and civil law cases

FOLLOW US ON:

Get in touch!

Addis Ababa, Ethiopia

ዋስትናን መንፈግ ህገ-መንግስታዊ መብት የሆነውን ( Rights on Presumption of Innocence) የሚጋፋ ስለመሆኑ……..

  • Home
  • Amharic Laws
  • ዋስትናን መንፈግ ህገ-መንግስታዊ መብት የሆነውን ( Rights on Presumption of Innocence) የሚጋፋ ስለመሆኑ……..

ወንጀሉ ክብደት እና ወንጀሉን ከፈፀሙበት ሁኔታና ክብደት አኳያ በዋስትና ቢወጡ ይመለሳሉ የሚል እምነት የለንም በሚል ምክነያት በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥረዓት አንቀፅ 67(1(ሀ)) መሰረት ዋስትናን መንፈግ በኢፌዲሪ ህገ መንግስት አንቀፅ 20(3) መሰረት የተሰጠን ከጥፋተኝነት ዉሳኔ በፊት እንደንፁህ ሁኖ የመገመት ህገ-መንግስታዊ መብት( Rights on Presumption of Innocence) የሚጋፋ ስለመሆኑ…….

ከወንጀሉ ክብደት እና ወንጀሉን ከፈፀሙበት ሁኔታና ክብደት አኳያ በዋስትና ቢወጡ ይመለሳሉ የሚል እምነት የለንም በሚል ምክነያት በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥረዓት አንቀፅ 67(1(ሀ)) መሰረት ዋስትናን መንፈግ በኢፌዲሪ ህገ መንግስት አንቀፅ 20(3) መሰረት የተሰጠን ከጥፋተኝነት ዉሳኔ በፊት እንደንፁህ ሁኖ የመገመት ህገ-መንግስታዊ መብት( Rights on Presumption of Innocence) የሚጋፋ ስለመሆኑ

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ከዚህ በፊት በመዝገብ ቁጥር 134228 በወንጀል ስነ- ስረዓት ህግ አንቀፅ 67 (1(ሀ)) ዋስትና ሊነፈግ የሚችልበትን ሁኔታ በተመለከተ በሰጠው አስገዳጅ የህግ ትርጉም የዋስትና መብት የሚነፈግባቸው ምክነያቶችን ፍርድቤቶች ከተለያየ ሁኔታዎች አንፃር እተመለከቱ ሊመዝኗቸው እንደሚገቡ እና አንድ ተከሳሽ የዋስትና መብት ቢከበርለት ግዴታውን የሚፈፅም የማይመስል ነው ተብሎ ግምት የሚወሰደው በቂ እና ህጋዊ ሊባሉ በሚችሉ ምክነያቶች ሊሆን እንደሚገባ፣ እንድሁም ምክነያቶቹ በቂ እና ህጋዊ ናቸው የሚለውን ጉዳይ በተመለከተ ማስረጃ የመመዘን ስልጣን ያላቸው የስር ፍርድቤቶች ከተለያዩ ከባቢያዊ ሁኔታዎች እና ከጉዳዩ ልዩ ባህሪ አንፃር ግንዛቤ ሊወሰዱ የሚገባ ስለመሆኑ አስገዳጅ የህግ ትርጉም ሰጥቶ የነበረ መሆኑ ይታወቃል፡፡

በዚህም የሰበር ሰሚ ችሎቱ ማስረጃን የመመዘን ስልጣን ስለሌለው በህግ ያልተከለከለን ዋስትና (በወንጀል ስነ-ስረኣት ህግ አንቀፅ 63 እና በሌሎችም ህጎች)፣ ነገር ግን  በወንጀል ስነ-ስረኣት ህግ አንቀፅ 67 ‹ሀ› መሰረት ፍርድቤቱ ዋስትናን  ለመከልከል በፖሊስም ሆነ ዓቃቢ-ህግ የቀረበው ዋስትና ይከልከልልን አቤቱታ  ‹‹ምክነያቱ በቂ ነው የሚባለው ‹‹ መቼ ነው ወይም ምን ሲሆን ነው የሚለውን በተመለከተ በግልፅ ከማስቀመጥ ይልቅ የስር ፍርድቤቶች እንደየነገሩ ሁኔታ ‹‹ Mutatis Mutandis ››  አንድ ተከሳሽ የዋስትና መብት ቢከበርለት ግዴታውን የሚፈፅም የማይመስል ነው ተብሎ ግምት የሚወሰድበትን ሁኔታ፤ ከተለያዩ ከባቢያዊ ሁኔታዎች እና ከጉዳዩ ልዩ ባህሪ አንፃር መዝነው ማስረጃ የመመዘን ስልጣናቸውን ተጠቅመው ዉሳኔ መስጠት ያለባቸው መሆኑን በማመላከት ዋስትና ለማስከልከል የቀረቡት ምክነያቶች ህጋዊ እና በቂ መሆን አለመሆናቸውን የስር ፍርድቤቶች መዝነው ዉሳኔ መስጠት ያለባቸው ስለመሆኑ በመግለፅ  አስገዳጅ ትርጉም ሰጥቷል፡፡

~~
ይሁን እንጂ የሰበር ችሎቱ ለወንጀል ስነ- ስረዓት ህግ አንቀፅ 67 (1(ሀ)) ድንጋጌ አተገባበር በቂ እና ህጋዊ ምክነያት የሚባሉት እና የማይባሉት የትኞቹ ናቸው የሚለውን ግልፅ ለማድረግ የሚስችል አመላካች ሁኔታዎችን ያላስቀመጠ እና ያልገለፀ በመሆኑ በዚህ እረገድ በስር ፍርድቤቶች ያለው አተረጓጎም እና አተገባበር ወጥ በሆነ መልኩ እንድፈፀም የሚያስችል የህግ ትርጉም አልነበረም፡፡ በዚህም መሰረት የወንጀል ስነ- ስረዓት ህግ አንቀፅ 67 (1(ሀ))

An application for bail shall not be allowed where: The applicant is of such nature that it is unlikely, that he will comply with the conditions laid down in the bail bond;

የሚለው አተገባበር በተለያዩ ፍርድቤቶች እና ችሎቶች የተለያዬ አረዳድ እና አሰራር ሲተገበር ቆይቷል ፤ በተለይ ደግሞ የዋስትና መብታቸው እንድፈቀድላቸው አቤቱታ የሚያቀርቡ ተከሳሾች የተከሰሱበት የህግ ድንጋጌ በፅኑ እስራት የሚያስቀጣ እና ከፍ ያለ ቅጣት የተቀመጠበት በሚሆንበት ግዜ የተከሰሱበት የህግ ድንጋጌ ከሚያስቀምጠው ቅጣት አንፃር ተከሳሾች የዋስትና ግደታቸውን ይወጣሉ የሚል እምነት የለንም በሚል ዋስትና እንድነፈግ የሚቀርብን አቤቱታ እንደ በቂ እና ህጋዊ ምክነያት በመውሰድ ዋስትናን መንፈግ ቁጥራቸው ቀላል በማይባሉ ፍርድቤቶች የተለመደ አሰራር እና አተረጓጎም ሁኖ ቆይቷል፤ በዚህም ምክነያት በኢፌድሪ ህገ-መንግስት አንቀፅ 19(5) የተደነገገው የተከሰሱ ሰዎች የዋስትና መብት እና ለዚህ መብት መኖር ቀዳሚ ምክነያት የሆነው በአንቀፅ 20(3) የተደነገገው ከፍርድ በፊት ንፁህ ሁኖ የመገመት መብትን የሚደነግጉት የህገ-መንግስት ድንጋጌዎች ተጥሰዋል ፡፡ ይህን መሰል ችግሮችን እና ወጥነት የተሳናቸው የአሰራር እና የአተረጓጎም ችግሮችን እልባት ለመስጠት በሚያስችል መልኩ ከዚሁ ጋር ተያይዞ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ጥቅምት 29 ቀን 2017 ዓ.ም (በሰበር መዝገብ ቁጥር 269430 ያልታተመ) ትርጉም ሰጥቷል፡፡

ይህን ጉዳይ አስመልክቶም ሰበር ሰሚ ችሎቱ የሰጠው አስገዳጅ የህግ ትርጉምም የወንጀል ህግ አንቀፅ 671(1) (‹ሀ› እና ‹ለ›) በመተላለፍ በከባድ ውንብድና ወንጀል በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ተሳትፈዋል ተብለው ተጠርጥረው የተከሰሱ ተከሳሾችን በተመለከተ በቀረበ የዋስትና ጥያቄ ላይ የስር ፍርድቤት አመልካቾች በዋስትና ቢወጡ የዋስትና ግደታቸውን አክብረው ሊቀርቡ የማይችሉ ስለመሆናቸው በቂ እና ህጋዊ ሊባሉ የሚችሉበትን ከባቢያዊ ሁኔታዎችን ሳያመለክት የተከሰሱበት የህግ ድንጋጌ ዋስትናን የሚከለክል ባይሆንም ከወንጀሉ ክብደት እና ወንጀሉን ከፈፀሙበት ሁኔታና ክብደት አኳያ በዋስትና ቢወጡ ይመለሳሉ የሚል እምነት የለንም በሚል ምክነያት ዋስትናን የመከልከሉን ህጋዊነት እና አግባብነት በተመለከተ ሰበር ችሎቱ በሰጠው ትንታኔ ላይ፤ ከወንጀሉ ክብደት እና ወንጀሉን ከፈፀሙበት ሁኔታና ክብደት አኳያ በዋስትና ቢወጡ ይመለሳሉ የሚል እምነት የለንም የሚለው ግምት ወደፊት በክርክር ሂደት የሚታይ ከመሆኑ በቀር ከጥፋተኝነት ዉሳኔ በፊት እንደንፁህ ሁኖ የመገመት መብታቸውን የሚጋፋ በመሆኑ ይህ አይነት ግምት በቂ እና ህጋዊ ግምት ባለመሆኑ የስር ፍርድቤት በወንጀል ሥነሥረዓት ህግ አንቀፅ 67 ‹ሀ› መሰረት ተከሳሾች የዋስትና መብት ቢከበርላቸው ግዴታቸውን የሚፈፅሙ የማይመስል ነው በማለት የስር ፍርድቤት የወሰደው ግምት ህጋዊ እና በቂ ምክነያት ባለመሆኑ ያለበቂ እና ህጋዊ ምክነያት በኢፌድሪ ህገ- መንግስት አንቀፅ 19(5) የተደነገገውን የዋስትና መብት መንፈግ ስለሆነ ከወንጀሉ ክብደት እና ወንጀሉን ከፈፀሙበት ሁኔታና ክብደት አኳያ በዋስትና ቢወጡ ይመለሳሉ የሚል እምነት የለንም በሚል ግምት ዋስትና መንፈግ መሰረታዊ የህግ ስህተት ነው በማለት የህግ ትርጉም ሰጥቷል፡፡

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በየመዝገብ ቁጥር 269430 ያልታተመ

ከፍትህ ድምፅ ገፅ ተወሰደ

Comments are closed

Compare Listings

Title Price Status Type Area Purpose Bedrooms Bathrooms