AleHig Law Office is a premier legal office specializing in a wide range of legal services in Ethiopia, Addis Ababa, including government engagement, corporate law, investment, commercial law, business law, property disputes, family law, succession, and civil law cases

FOLLOW US ON:

Get in touch!

Addis Ababa, Ethiopia

ብዙዎች ህግ የለም ብለው በደመነፍስ ሲመሩ፣ እኔ ግን በዚያው ጨለማ ውስጥ ብርሃን ሆኖ የሚታየውን ሕግ መኖሩን ለማሳየት #እየሞከርኩ ነው።

  • Home
  • Uncategorized
  • ብዙዎች ህግ የለም ብለው በደመነፍስ ሲመሩ፣ እኔ ግን በዚያው ጨለማ ውስጥ ብርሃን ሆኖ የሚታየውን ሕግ መኖሩን ለማሳየት #እየሞከርኩ ነው።

በብዙዎች ዘንድ #ሕግ የለም” የሚል ተስፋ መቁረጥ በነገሰበት፣ ገንዘብ ካለህ ሕግ አያስፈልግህም የሚል የተሳሳተ ብሂል በሰፈነበት ሁኔታ ውስጥ ቆሜ፣ እኔ ግን አንድ እውነትን ለማረጋገጥ ደጋግሜ እተጋለሁ። አዎ፣ #እየሞከርኩ ነው‼️
አለሕግ እና ሕግ አለ
ብዙዎች ህግ የለም ብለው በደመነፍስ ሲመሩ፣ እኔ ግን በዚያው ጨለማ ውስጥ ብርሃን ሆኖ የሚታየውን ሕግ መኖሩን ለማሳየት #እየሞከርኩ ነው።
ሕግ መኖሩ ብቻውን በቂ አይደለም፤ ሕጉ ለሁሉም እኩል መሆኑን እና ማንም ከሕግ በላይ አለመሆኑን በተግባር ለማሳየት የፍትህ ስርዓቱ ላይ የራሴን አሻራ ለማሳረፍ እተጋለሁ። ይህ ጥረቴ ለዛሬ ብቻ ሳይሆን፣ ለሀገሬ መፃኢ እድል እና ለልጆቻችን የሚተርፍ የፍትህ መሠረት ለመጣል ነው።

ሕግ መኖሩን እያወቁ፣ ነገር ግን እንደሌለ በማስመሰል የሰውን ንብረትና ሀብት ለዘረፉ፣ “ሕግ አለ!” ብዬ ፊት ለፊት እጋፈጣቸዋለሁ። የኔ ሙከራ እንደ አንድ ተራ ጠበቃ የሙያ ግዴታን መወጣት ብቻ አይደለም።

እኔ እየሞከርኩ ያለሁት፦
✔️ ለተገፉት ድምፅ ለመሆን፣
✔️ለተካዱት እውነትን ለማውጣት፣
✔️ ለተጭበረበሩት መብታቸውን ለማስከበር ነው።
የእነሱ ህመም ህመሜ፣ ስብራታቸው ስብራቴ ሆኖ ከጎናቸው እቆማለሁ። የተሰበረውን ፍትህ ለመጠገን እኔው ራሴ ተሰብሬም ቢሆን የቆሙለትን ዓላማ ዳር ለማድረስ እጥራለሁ።

በዚህ ሂደት ውስጥ መረጃ የፍትህ ዋስትና መሆኑን ለማስረፅ እሰራለሁ። ያለ መረጃ የሚጮህ ድምፅ ሰሚ እንደማያገኝ አውቃለሁና፣ እውነትን በመረጃ ደግፌ ለማቅረብ እና እያንዳንዱ የፍትህ ሂደት በስርዓትና በሕግ እንዲመራ ለማሳመን ሌት ተቀን #እየሞከርኩ ነው።

አዎ፣ ዛሬም ነገም #እየሞከርኩ ነው! #አለሕግ የሚለውን ድምፅ በ “ሕግ አለ” ለመተካት፣ በሀገሬ ላይ የሕግ የበላይነት እንዲነግስ እንደ አንድ ዜጋ የድርሻዬን እወጣለሁ። ግፍና መካድ በጊዜያዊነት ቢያሸንፉም፣ በመጨረሻ ግን ሕግና ስርዓት ማሸነፋቸው አይቀሬ ነው።
አዎ! ሕግ አለ!! ‼️🙏 እየሞከርኩ ነው …….✍️

ሚኪያስ መላክ በማናቸውም ፍርድ ቤት ጠበቃ እና ህግ አማካሪ
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Compare Listings

Title Price Status Type Area Purpose Bedrooms Bathrooms