AleHig Law Office is a premier legal office specializing in a wide range of legal services in Ethiopia, Addis Ababa, including government engagement, corporate law, investment, commercial law, business law, property disputes, family law, succession, and civil law cases

FOLLOW US ON:

Get in touch!

Addis Ababa, Ethiopia

የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ለማግኘት መቅረብ ያለባቸው ማስረጃዎች

  • Home
  • Daily Advice
  • የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ለማግኘት መቅረብ ያለባቸው ማስረጃዎች

በጣት አሻራ የተደገፈ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ለመያዝ ለማግኘት መቅረብ ያለባቸው ማስረጃዎች፡-

ሀ/ በግለሰብ ከሚካሄድ የንግድ ስራ፣ ከተቀጣሪ እና የሙያ ስራ ከሚሰራ ሰው፡-
👉 የግብር ከፋዩ የከተማ ቀበሌ ወይም የቀበሌ ገበሬ ማህበር መታወቂያ፣
👉 የአመልካቹ /የግብር ከፋዩ/ ፎቶግራፍ፣
👉 አመልካቹ የቤተሰቡን ንግድ የወረሰ አካለ መጠን ያልደረሰ ልጅ ሞግዚት ከሆነ ይህንኑ የሚያረጋግጥ ከፍ/ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡

ለ/ ኩባንያዎች፣ አክሲዮን ማህበራት፣ የሽርክና ማህበራት፣ የአሽሙር ማህበራት /joint venture/ እንዲሁም በንግድ ስራ የተሰማሩ ማናቸውም ማህበራት፡-
👉 የማህበር መመስረቻ ፅሁፍና መተዳደሪያ ደንብ፣
👉 የድርጅቱ ዋና ስራ አስኪያጅ ከስድስት ወር ወዲህ የተነሳው ፎቶግራፍና በግሉ ያወጣውን የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣
👉 አመልካቹ ወኪል ከሆነ ስለ ውክልናው የተሰጠውን ሕጋዊ ማስረጃ፣
👉 ከማህበረተኞቹ መካከል የውጭ አገር ዜጋ ካለ ማንነቱን የሚገልጽ ፓስፖርት ኦርጅናልና ፎቶ ኮፒ እንዲሁም ከኢንቨስትመንት ጽ/ቤት የተሰጠ ማስረጃ፣

ሐ/ የመንግስት የልማት ድርጅቶች፡-
👉 የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣
👉 ድርጅቱ የተቋቋመበት ደንብ፣
👉 የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ ምደባ ደብዳቤ፣
👉 የሥራ አስኪያጁ የቀበሌ መታወቂያ፣ ፎቶግራፍና በግሉ ያወጣውን የግብር ከፋይ ከፋይ መለያ ቁጥር፣

መ/ የመንግስት ባለ በጀት መስሪያ ቤቶች
👉 የማቋቋሚያ አዋጅ ወይም ደንብ፣
👉 መስሪያ ቤቱ የሚወክለው ሰው የውክልና ደብዳቤና የግለሰቡ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር።

ሠ/ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች
👉 የፍትሕ ሚኒስቴር የምዝገባ ምስክር ወረቀት፣
👉 የሥራ አስኪያጅ ምደባ ደብዳቤና የግሉን የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር።

ረ/ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ለማግኘት መሟላት ያለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች/ግዴታዎች
👉 የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ለማግኘት በባለስልጣኑ ወይም በሌሎች ኃላፊነቱ በተሰጣቸው መ/ቤቶች የተዘጋጀውን ቅጽ ሞልቶ የማቅረብና የጣት አሻራ የመስጠት፣
👉 የንግድ ስራ ፈቃድ ለማውጣት የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የምስክር ወረቀት ከባለስልጣኑ ወይም ሥልጣን ከተሰጣቸው መ/ቤቶች በቅድሚያ የማግኘት፣
ማሳሰቢያ፡- ግለሰቡ የተለያየ የንግድ ዘርፍ ወይም ቅርንጫፎች በተለያዩ ቦታዎች ቢኖሩትም አንድ ግብር ከፋይ ማውጣት ያለበት አንድ መለያ ቁጥር ብቻ ነው።
ገቢዎች ሚኒስቴር
የሕግ አማካሪ እና ጠበቃ
+251920666595
አማራጭ የሕግ እውቀት አለ
Alternative legal enlightenment/ALE
Telegram
https://t.me/AleHig

Telegram_Group
https://t.me/AleHig_Group

Instagram
https://www.instagram.com/alehigofficial

YouTube
https://www.youtube.com/@Ale_Hig

LinkedIn
https://www.linkedin.com/company/alehig/

Website
https://www.alehig.com

Email address
Alehig7@gmail.com

Telegram Bot
@LawsocietiesBot

Comments are closed

Compare Listings

Title Price Status Type Area Purpose Bedrooms Bathrooms