AleHig Law Office is a premier legal office specializing in a wide range of legal services in Ethiopia, Addis Ababa, including government engagement, corporate law, investment, commercial law, business law, property disputes, family law, succession, and civil law cases

FOLLOW US ON:

Get in touch!

Addis Ababa, Ethiopia

በተለያየ ጊዜ የጥብቅና ፈቃድ ለማግኘት የተፈተኗቸው ጥያቄዎች!

  • Home
  • Case Studies
  • በተለያየ ጊዜ የጥብቅና ፈቃድ ለማግኘት የተፈተኗቸው ጥያቄዎች!

የጥብቅና ፈቃድ ማረጋገጫ ፈተናዎች

1.የህገ መንግስቱን መሰረታዊ መርሆዎችን ዘርዝር።
2.በአጭር ሥነ-ሥርአት እና በተፋጠነ ሥነ-ሥርአት የሚቀርቡ ጉዳዮችን ዘርዝር።
3.ፍርድ ቤት የራሱን ውሳኔ የሚያይባቸው ሁኔታዎች ምንምን ናቸው።
4.ይቅርታና ምህረት ልዩነቱ ምንድነው።
5.በአስገዳጅ ሁኔታ እና በህጋዊ መከላከል መሀከል ያለው አንድነት እና ልዩነት ምንድነው።
6.ቀብድ የተቀበለ ሰው ውሉን ለማቋረጥ ቢፈልግ ምን ማድረግ አለበት።
7.ሰራተኛ በራሱ ያለ ማስጠንቀቂያ ስራ ሊያቋርጥ የሚችልባቸው ሁኔታዎች መንድናቸው።
8.ሁለቱ አይነት የቅጣት ገደቦች አንድነት እና ልዮነት።የሚፈቀድባቸው እና የሚከለከልባቸው መንገዶችን አስቀምጥ።
9.በአስቸኳይጊዜ አዋጁ የማይታገዱ የህገ መንግስቱ አንቀጾች የትኞቹ ናቸው።
10.የውል መሰረዝ እና መፍረስ አንድነት እና ልዩነት።
11.ለመሰየም የሚፈቀድበት እና የሚከለከልበት መስፈርት።
12.አስቦ እንድ ሰው ወንጀል አድርጎ የማይቀጣው መቼ ነው።
13.ፍርድ ቤት ቅጣትን በመሰለው የሚያቀልባቸው የወንጀል ህግ አንቀጾች የትኞቹ ናቸው።
14.ተደራራቢ ወንጀሎችን አይነት ዘርዝር።አንድነት እና ልዩነታቸውስ።
15.ልዩ የቅጣት ማክጃ እና ማቅለያ የሚባሉት የትኞቹ ናቸው።

  1. በወንጀል ስነስርአት ይግባኝ የማይባልባቸው ጉዳዮችን ዘርዝር
    17.የአስተዳደር ውል እና መደበኛ ውል ልዩነት።
    18.እዳ ሚከፈልበት ጊዜ ቅደም ተከተሉ…..ማለት ለሰራተኛ የሚከፈል፣ለግብር የሚከፈል፣ለቀለብ የሚከፈል የቱ ይቅደም።
    19.ለውርስ ያልተገባ መሆን እና ከውርስ መነቀልን አብራራ።
    20.የቅጣት ይርጋ እና የክስ የርጋን በወንጀል አብራራ።
    21.ከውል መፈጸም ጋር በተያያዘ ተዋዋዮች በተናጠል ውል መሰረዝ(unilateral  cancelations) የሚችሉባቸው ሁኔታዎች ምድናቸው።
    22.በስውር የተደረገ ይዞታ እና በማያሻማ አይነት የተደረገ ይዞታ ልዩነት እና አንድነት።
    23.የመልካም ጸባይ ዋስትናን መርህን አብራራ።
    24.የወንጀል ህግ ግብ እና አላማ አስቀምጥ።
    25.ክስ ወደሌላ ስፍራ የሚዛወርባቸው ምክንያቶች የትኞቹ ናቸው።
    26.በጋብቻ እና እንደ ባልና ሚስት መኖር ያላቸው አንድነት እና ልዮነት።
    27.በፍርድ መከልከል እና ህግ መከልከል ልዩነት እና አንድነት።
    28.ጋብቻ ከፈረሰ በኃላ አንዲት ሴት 180 ቀን ሳይሞላት ማግባት የምትችለው መቼ ነው።
    29.ጋብቻ ለመፈጸም መሟላት ያለባቸው ቅድመ ሁኔታዎችን ዘርዝር።
    30.ጋብቻ የሚፈርስባቸው 4ቱ ምክንያቶች የትኞቹ ናቸው።
    ጋብቻ በተጋቢዎች ግላዊ ግንኙነት ላይ የሚኖረውን ውጤት ዘርዝር።
    31.ለውርስ ያልተገባ ሰው ሟችን ሊወርስ የሚችልበት exceptions ምድን ናቸው።
    32.አንድ ግዴታ እንዲፈጸምለት የሚጠይቅ ሰው ለግዴታው መኖር ማስረዳት አለበት(one who alleged the fact has to proof it)ለሚለው የህግ መርህ በወንጀልም ይሁን ፍትሐብሆር ያሉ exception ኖችን ዘርዝር።…..ለምሳሌ የውርስ ህግ 896፣ የወንጀል ህግ 35።
    33.ፍርድ ቤት አንድን ሰው ጥፋተኛ ካለ በሓላ ከቅጣት በፊት ወንጀሉ በይርጋ የቀረ መሆኑን ቢያውቅ መዝገቡን በይርጋ መዝጋት አለበት ወይስ በይግባኝ ነው ሊታረም የሚገባው የወንጀል ህግ 216(2)።
    34.ውልን በግዴታ እንዲፈጸም ለማዘዝ የሚቻለው መቼ ነው። የፍ/ህ 1776።
    35.የወንጀል አፈጻጸም ደረጃዎችን ዘርዝር።አንቀጽ 26 እና ተከታዩ
    36.የህግ ሰውነት የተሰጣቸው ድርጅቶች የሚቀጡባቸውን የወንጀል ህግ ልዩ ክፍሎች ዘርዝር።
    37.ከአድማ እና አምባጎሮ ውጭ ህብረት የሚፈጸሙ ወንጀሎች እንዴትያሉ ናቸው።
    38.በህገ መንግስቱ ሰብአዊ መብት ተብለው የተዘረዘሩት ቢያንስ 10 ጥቀስ።
    38.በወንጀል ፍትህ ስርአቱ የተጎጂዎች መብት የሚባሉትን ዘርዝር…..ለምሳሌ ካሳ የማግኘት መብት፣ጥበቃ የማግኘት መብት…..።
    40.የፍርድ ቤቶችን የየእለት ተግባራት ዘርዝር….ለምሳሌ
    የህግ የበላይነትን ማረጋገጥ
    ሰብአዊ መብቶች እና መሰረታዊ ነጻነቶችን ማስከበር
    በህግ መሰረት መሰራቱን ማረጋገጥ(due process )
    41.የዳኝነት ተጠያቂነት አይነቶች ዘርዝር….ለምሳሌ
    በይግባኝ ተጠያቂነት
    የህዝብ (የፓርላማ) ተጠያቂነት
    42.ለአንዱ መብት ለአንዱ ግዴታን ሚያቋቁም ውል ላይ ከሁለቱ አንዱ ባይፈርሙ ውሉ ምን ይሆናል።
    43.የፍትሀብሄር ስነስአት ህጉ 343 ህጉ እና ልምዱ ምንድነው።
    44.አዲሱ የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ የያዛቸው አዲስ ሀሳቦች ምን ምን ናቸው?
  2. የቀዳሚ ምርመራ ክስ

Comments are closed

Compare Listings

Title Price Status Type Area Purpose Bedrooms Bathrooms