AleHig Law Office is a premier legal office specializing in a wide range of legal services in Ethiopia, Addis Ababa, including government engagement, corporate law, investment, commercial law, business law, property disputes, family law, succession, and civil law cases

FOLLOW US ON:

Get in touch!

Addis Ababa, Ethiopia

ህግን አለማወቅ እና የህግ ስህተት ከተጠያቂነት የማያድን መሆኑ ያውቃሉ ?

  • Home
  • Daily Advice
  • ህግን አለማወቅ እና የህግ ስህተት ከተጠያቂነት የማያድን መሆኑ ያውቃሉ ?
  • የህግ ምንነት
    ህግ የሚለው ቃል በማህበረሰቡ ዘንድ በስፋት የሚታወቅ ቃል ነው፡፡
    በተለይ ህግ አስገዳጅ መሆኑን የሚረዳው ለመሆኑ ቀደም ባለው ጊዜ በየዕለት ኑሮ ፀብ ሲገጥመው እንኳን “በህግ አምላክ” ብሎ ፀብ የማብረድ ልምድ የነበረው መሆኑ ማሳያ ነው፡፡ ሆኖም ማህበረሰቡ ህግን የሚረዳው በተለምዶአዊው አረዳድ እንጂ የዘርፉ ባለሞያዎች በሚረዱበት መልኩ አይደለም፡፡

በመሰረቱ ህግ ለሚለው ቃል ትርጓሜ መስጠት ቀላል አይደለም፡፡ ምክንያቱም የተለያዩ ምሁራን ቃሉን በተለያየ መንገድ የሚገልፁት በመሆኑ ነው፡፡ እንዲሁም የቃሉ ፍቺ ሊደረስባቸው በሚፈለጉት የተለያዩ ዓላማዎች ምክንያት ሊለያይ ይችላል።
ለህግ ቃላት ትርጉም በመስጠት የሚታወቀው ብላክስ ሎው የህግ መዝገበ ቃላት በተሻሻለው ስድስተኛ እትሙ (Black’s Law Dictionary, 6th ed.,) ለህግ ትርጉም ሲሰጥ law is “a body of rules of action or conduct prescribed by controlling authority, and having binding legal force, which must be obeyed and followed by citizens subject to sanctions or legal consequence is a law.” ወደ አማርኛ በግርድፉ ሲመለስ ስልጣን ባለው አካል የተደነገገ የተግባር ወይም የምግባር ደንብ እና አስገዳጅ የህግ ኃይል ያለው አካል ነው። ይህንንም ዜጎች ሊታዘዙት እና ሊከተሉት የሚገባ ሆኖ ማዕቀብ ወይም ህጋዊ ውጤት የሚጥል ህግ መሆኑን መረዳት ይቻላል።

በመሆኑም የአንድ ሀገር ሕግ፡- ሰላምን ለማስጠበቅ፣ ነባራዊ ሁኔታውን ለማስጠበቅ (maintain the status quo)፣ የግለሰብ መብቶችን ለማስጠበቅ፣ አናሳዎችን ከብዙኃን ለመከላከል ( protect minorities against majorities)፣ ማኅበራዊ ፍትህን ለማስፈን( promote social justice) እና ሥርዓት ያለው ማህበራዊ ለውጥ እንዲኖር ለማድረግ( provide for orderly social change) ያገለግላል።

  • የህግ መሰረታዊ ባህሪያት
    የህጎችን የተለመዱ ባህሪያት እና ተፈጥሮ መፈተሽ የህግ ጽንሰ-ሀሳብን ለመገንዘብ የሚረዳ ሲሆን ከእነዚህ ባህሪያት እና ተፈጥሮዎች መካከል እንደ ወሰኝ ወይም አስፈላጊ የሚታሰቡት አጠቃላይነት(ህግ በሁሉም ሰው ላይ በተመሳሳይነት (uniformity) እና እኩልነትን (Equality) የሚፈፀም መሆኑ)፣ መደበኛነት (ህግ ማህበራዊ ባህሪን በመፍቀድ፣ በማዘዝ ወይም በመከልከል ልማዶችን የሚፈጥር መሆኑ) እና ማዕቀብ ወይም ቅጣትን (ህግን ያላከበረ ቅጣት የሚጠብቀው መሆኑን) ያካትታሉ፡፡
  • ህግን አለማወቅ እና የህግ ስህተት ከተጠያቂነት የማያድን መሆኑ
    በወንጀልም ሆነ በፍትሐ ብሄር ጉዳይ ህጎቹ ስልጣን ባለው የህግ አውጪ አካል ወጥተው ከፀደቁበት ቀን ጀምሮ በስራ ላይ እንደሚውሉ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም ዜጎች የህጎቹን መኖር ወይም መውጣት የማወቅ ግዴታ አለባቸው፡፡ ይኸውም ህግን አለማወቅ ከተጠያቂነት አያድንም የሚለው የህግ መርህ በላቲን Ignorantia juris non excusat ወይም በእንግሊዘኛ “ignorance of the law excuses not” ከሮማውያን ህግ የተወሰደ ሲሆን ህግን የማያውቅ ሰው ይዘቱን ባለማወቅ ብቻ ህጉን በመተላለፍ ከተጠያቂነት ሊያመልጥ እንደማይችል የሚገልጽ የህግ መርህ ነው። እንዲሁም የህግ ስህተት (mistake of law) ሰዎች በአንድ ጉዳይ ላይ ተፈጻሚነት ያለው ሕግ እንዴት እንደሚተገበር የሚይዙትን የአረዳድ ስህተቶችን የሚያመለክት የሕግ መርህ ነው። ‘ህግን አለማወቅ’ እና ‘የህግ ስህተት’ የሚሉት ቃላቶች በህጋዊ እይታ ውስጥ ተመሳሳይ ትርጉም የማይሰጡ ሲሆን አለማወቅ ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ አጠቃላይ የእውቀት ያለመኖርን ያመለክታል። ማሳሳት ግን እውቀትን ተቀብሎ ወይም እውቀት እንዳለ አምኖ ነገር ግን የተሳሳተ መደምደሚያን ላይ መድረስን ያሳያል። ይሁንና ህግን አለማወቅም ሆነ የህግ ስህተት ከተጠያቂነት እንደማያድን እንደ አንድ የህግ መርህ ይወሰዳል፡፡
  • ህግን አለማወቅ እና የህግ ስህተት ከተጠያቂነት የማያድን መሆኑ መርህ ምክንያት (rationale for “ignorance of the law excuses not” principle)
    በመሠረቱ አንድ ሰው ህግን ከጣሰ ህጉን ስለመጣሱ ምንም እውቀት ባይኖረውም ተጠያቂ ይሆናል ማለት ነው፡፡ ይህ ማለት ሰዎች ህጉን አላውቀውም በማለት ድርጊታቸውን ሊከላከሉ እንደማይችሉ ያመለክታል፡፡ የዚህ ህግ መርህ ምክንያት( rationale) አለማወቅ ሰበብ ቢሆን ኖሮ ምንም እንኳን ያ ሰው ህጉ መኖሩን ቢያውቅም በወንጀል ህግ ወይም በፍትሐ ብሄር ጉዳይ ቢከሰስ ህጉን አላወኩም በማለት ከተጠያቂነት ማምለጫ እንዳይሆን በሚል ነው፡፡ በመሆኑም ከመርህ በስተጀርባ ያለው ምክንያት አለማወቅ ሰበብ ከሆነ ማንኛውም በወንጀል ወይም በፍትሐ ብሄር የተከሰሰ ሰው ተጠያቂነትን ለማስወገድ አላዋቂ ነኝ ሊል ይችላል የሚል ነው። ስለዚህ ህጉ የቱንም ያህል አጭር ጊዜ ቢቆይ ሁሉም ህጎች በስልጣኑ ውስጥ ላለ ለእያንዳንዱ ሰው ተፈፃሚ ይሆናሉ ማለት ነው፡፡

በኢትዮጵያም ህግን አለማወቅ ወይም የህግ ስህተት ከተጠያቂነት እንደማያድን በወንጀል ህጉ አንቀፅ 81 ስር ተደንግጓል፡፡ በዚሁ መሰረት ሕግን አለማወቅ ወይም በህግ ላይ መሳሳት መከላከያ ሊሆን እንደማይችል ያስቀምጣል፡፡ በሌላ በኩል በፍትሐ ብሄር ህግ አንቀፅ 2035/1 እና 2 ስር አንድ ሰው በህግ ላይ በትክክል የተገለፀውን ድንጋጌ፣ ልዩ ደንብና ሥርዓት የጣሰ እንደሆነ ጥፋተኛ እንደሆነ እና ህግን አለማወቅ ይቅርታ ሊያስገኝ የማይችል መሆኑ ተደንግጎ ይገኛል፡፡

  • የህግ መኖር ማወቅ የሚቻልበት መንገድ
    ህግን አለማወቅ ከተጠያቂነት አያድንም የሚል የህግ መርህ ተቀባይነት አለው ማለት ሁሉም ሰው ህግ የማወቅ ግዴታ እንዳለበት እና የህግን መኖር ያውቃል የሚል ግምት እንደሚወሰድ ያመለክታል፡፡ ታዲያ ሁሉም ሰው ህግን የተማረ ሊሆን የማይችል በመሆኑ እንዲሁም ህግን ቢማር እንኳ ሁሉን ህግ በተገቢው ሁኔታ ያውቃል ማለት ተጨባጭ (realistic) የማይመስል በመሆኑ የህግን መኖር እንዴት ማወቅ ይቻላል የሚለው ወሳኝ ጥያቄ ነው፡፡

የህግን መኖር በተለያዩ መንገዶች ማወቅ ይቻላል፡፡ ይኸም በዋናነት ህጎች የሚፀኑበትን ጊዜ ከሚገነግጉ ድንጋጌዎች ሲሆን ህግ የሚፀናበት ጊዜ በተለያዩ ህጎች ላይ በተለያየ ሁኔታ ተገልፆ ይገኛል፡፡ በዚሁ መሰረት ህጉ ወይም አዋጁ በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከሚወጣበት ቀን ጀምሮ የሚፀና ይሆናል፣ ህጉ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከፀደቀበት ቀን ጀምሮ ተፈፃሚ ይሆናል እና የተወሰነ ቀን በማስቀመጥ ከዛ ቀን ጀምሮ ተፈጻሚ እንደሚሆን ሊደነገግ ይችላል፡፡ ለምሳሌ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገ መንግስት በህዳር 29/1987 የፀደቀ ሲሆን ከነሐሴ 15/1987 ጀምሮ በሥራ ላይ እንደሚውል እና የፀና እንደሚሆን በመደንገግ ህጉ የሚፀናበትን ጊዜ በዚህ መልኩ አውጇል ፡፡ በመሆኑም ህጎቹ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ታውጀው ከፀደቁበት ቀን ጀምሮ ወይም በነጋሪት ጋዜጣ ታትመው ከወጡበት ጊዜ ጀምሮ በህብረተሰቡ ይታወቃሉ ተብሎ ይገመታል፡፡

አማራጭ የሕግ እውቀት አለ
Alternative legal enlightenment/ALE ጠበቃና #የሕግአማካሪ

WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
ነፃ የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ የሕግ መረጃና መሰረታዊ የሕግ እውቀት ያገኛሉ

አማራጭ የሕግ እውቀት አለ Alternative legal enlightenment/ALE
Alternative legal enlightenment/ALE

Comments are closed

Compare Listings

Title Price Status Type Area Purpose Bedrooms Bathrooms